ምሳሌ: የኤክስቼንጅ ሰርቨርስ

አጠቃላይ ስታትስቲክስ · ተከታታይ ጊዜ

ባለፈው ሳምንት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ እንደ CVE-2023-36439 ታግ ተሰጥቷቸው በየቀኑ ምላሽ ሲሰጡ የተገኙ የ IPv4 & Ipv6 አድራሻዎች ብዛትን የሚያሳይ ስታክድ ግራፍ።

አጠቃላይ ስታትስቲክስ · ምስላዊ ዕይታ · ሰንጠረዥ

ባለፈው ቀን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ እንደ CVE-2023-36439 ታግ ተሰጥቷቸው በየቀኑ ምላሽ ሲሰጡ የተገኙ የ IPv4 & Ipv6 አድራሻዎች ብዛትን የሚያሳይ ሰንጠረዥ።

አጠቃላይ ስታትስቲክስ · የዛፍ ካርታ

ከሀገር ስፋት ጋር በተመጣጣኝነት በተወከለ ቁጥር፣ እንደ CVE-2023-36439 ታግ ተሰጥቷቸው በተወሰነ ቀን የተገኙ የ IPv4 & Ipv6 አድራሻዎች ብዛትን የሚያሳይ የዛፍ ካርታ።

የሀገር ቁራሽ ክፍል ላይ ጠቅ ማድረግ የሶርሶች ብትን ዝርዝርን ሲደመር አጠቃላይ ስታቲስቲክስን ከ CIA world factbook ላይ ይሰጣል።

ምሳሌ: የተጋለጡ የ CWMP መሣሪያዎች

አጠቃላይ ስታትስቲክስ · ተከታታይ ጊዜ

በሳውዲ አረቢያ በየቀኑ የሚጋለጥ የ CWMP መሣሪያ IP አድራሻዎችን ቁጥር የሚያሳይ የ 2 ዓመት ዋጋ ያለው የታሪካዊ ውሂብ የጊዜ መስመር (በፐብሊክ ዳሽቦርድ ላይ ያለ ከፍተኛው ጊዜ)።

ማስታዎሻ፡- ይህ ግራፍ እ.ኤ.አ በጃንሪ 2023 መጨረሻ ላይ ከ CWMP ተጋላጭነት አንፃር መሻሻልን አሳይቷል።

ምሳሌ: MISP አብነቶች

የ IoT መሳሪያ ስታትስቲክስ · ምስላዊ ዕይታ · የአሞሌ ቻርት

በርከት ያሉ መሣሪያዎች እና የሶፍትዌር ሶልዩሽኖች በስካኒንግ ጊዜ ፊንገርፕሪንት ሊደረጉ ይችላሉ። ይህ ግራፍ የሚያሳየው (በሎጋሪዝም ስኬል) ባለፈው ወር፣ በየአንዳንዱ የ MISP አብነት አሂድ (instances running) በአማካይ በየቀኑ የተገኙ የ IP አድራሻዎችን ቁጥርን ነው።

ምሳሌ: ለብዝበዛ የተዳረጉ ተጋላጭነቶች

የጥቃት ስታትስቲክስ:- ተጋላጭነት · ክትትል

ባለፉት ቀናት የመጀመሪያዎቹ 100 የተገኙ ሙከራ የተደረገባቸው የብዝበዛ ተጋላጭነቶች (ከሀኒፖት ሻዶሰርቨር ማሳያዎች ውስጥ)፣ መጀመሪያ ላይ በልዩ ጥቃት ሰንዛሪ IP’s እንዲደረደሩ የተደረጉ።

የካርታ አማራጩን ጠቅ ማድረግ ተጠቃሚው በ"ሶርስ" እና "መዳረሻ" ሆስት ዓይነቶች መካከል እንዲቀያይር ያስችለዋል (ማለትም በአጥቂው IP ጂኦግራፊያዊ መገኛ እና በሀኒፖት IP ጂኦግራፊያዊ መገኛ መካከል)።

ማስታወሻ፡- የጥቃት ሰንዛሪው ጂኦግራፊያዊ መገኛ የአጥቂውን መገኛ ቦታ በትክክል ሊወክል ወይም ላይወክል ይችላል።

ምሳሌ: ኩነቶችን መተርጎም

ክስተቶችን ለመተርጎም ዳሽቦርዱን መጠቀም፡- ባልተለመደ መልኩ እየጨመረ የመጣ በግብፅ ተጋላጭ ሆኑ የ CWMP መሣሪያዎች (የ Huawei ሆም ራውተሮች እንደሆኑ የሚታመኑ)፣ ይህንንም ተከትሎ ከተመሳሳይ ሀገር የሚነሱ የሚራይ ጥቃቶች።

ማስታዎሻ፡- ሻዶሰርቨር ለማሳወቅ እና የእርምት እርምጃ ለመውሰድ ከግብፅ nCSIRT ጋር ሰርቷል።

የ IoT መሳሪያ ስታትስቲክስ · ተከታታይ ጊዜ

እ.ኤ.አ በ 2023-01-05 እና በዚህ ቀን አካባቢ ይፋ እንደተደረገው በግብፅ መሠረተ ልማት ላይ የተጋለጡ የ IoT መሣሪያዎች መጠን መጨመሩን ምልከታ ተደርጓል።

ጥያቄ

የ IoT መሳሪያ ስታትስቲክስ · የዛፍ ካርታ በሻጭ

በቀናት ወደ ኋላ እና ወደ ፊት በመሄድ መሣሪያዎቹ የ 2023-01-05 አዲሶቹ ግልፅ የ Huawei መሣሪያዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ያሳያል።

ጥያቄ

አጠቃላይ ስታትስቲክስ · ተከታታይ ጊዜ

በስካኒንግ ወቅት የታየ የ CWMP ግኝቶች ሹል ከፍታ (spike) በ 2023-01-05 ከተከሰተው ሹል ከፍታ (spike) ጋር ዝምድና/ግንኙነት አለው።

ጥያቄ

የሻዶሰርቨር ሀኒፖትስ ሴንሰሮች የሚራይ እና ብሩት ፎርስ ጥቃቶችን በመሰንዘር ጥቃት ሊደርስባቸው የሚችሉ የግብፃዊያን መሳሪያዎችን ለይተዋል።

ጥያቄ

እንዲሁም ከግብፅ ለጥቃት የተጋለጡ መሳሪያዎች የሚሰነዘሩ ተዛማጅ የ ቴልኔት ብሩት ፎርስ ጥቃቶችን ለይተዋል።

ጥያቄ

ብዙ ሶርሶች መጠቀም እንዲሁም የታግ እና ኦቨርላፒንግ አማራጮችን መምረጥ ምልከታዎቹ በተመሳሳይ ግራፍ ላይ እንዲታዩ ያስችላቸዋል።

ጥያቄ

ምሳሌ: ልዩ ሪፖርቶች

አልፎ አልፎ ሻዶሰርቨር በዓይነታቸው ልዩ የሆኑ ዘገባዎችን ያወጣል። ውሂቡን በ ኤክስ/ትዊተር እና በድረ-ገፃችን እናሳውቃለን - ነገር ግን ከክስተቱ በኋላ ወሳኝ የሆኑ ቀናትን ማወቅ ይፈልጉ ይሆናል። ቀናቶቹን ለማግኘት የሚቻልበት አንዱ መንገድ በጊዜ ተከታታይ ቻርት ላይ የልዩ ዘገባ ቀኖችን በመፈለግ ይሆናል - እናም እነዚያን ቀኖች ለአንድ ቀን ስታቲስቲክስ ይበልጥ ምቹ ወደሆኑ (እንደ ካርታዎች ወይም የዛፍ ካርታዎች ያሉ) ሌሎች ውክልናዎች ማስተላለፍ ይችላሉ። ልዩ ዘገባዎች በዳሽቦርዱ ላይ የምንጭ ስብስብ special የሚል ቃል አላቸው።

የጊዜ ተከታታይ ቻርትን በመጠቀም ልዩ ዘገባዎችን መፈለግ፡-

ጥያቄ

ለምሳሌ የዛፍ ካርታ ልዩ ዘገባ እ.ኤ.አ በ 2024-01-29 ተገኝቷል፡-

ለልዩ ዘገባዎች ዝርዝር እባክዎን የዘገባዎች ዝርዝርን ይቃኙ በእኛ ዋና ድር ጣቢያ ልዩ ዘገባዎች በስማቸው ውስጥ "ልዩ" የሚል ይኖራቸዋል።

ምሳሌ: የጊዜ ተከታታይ ቻርቶች

ቶግሊንግ ሀይ ኮንትራስት

የውጤት የጊዜ ተከታታይ ቻርቶች በነባሪነት ለአክሲስ መስመሮች ፈዘዝ ያለ ግራጫ ቀለም አላቸው። “ቶግሊንግ ሀይ ኮንትራስት” የሚለውን በመምረጥ የአክሲስ መስመሮቹን ጥቁር ማድረግ ይቻላል - ይህም ዘገባዎች ላይ ለማራባት ቀላል ሊደርገው ይችላል።

ቶግሊንግ ቪዚቢሊቲ

ብዙ ተከታታይ ውሂብ በጊዜ ተከታታይ ቻርት ላይ ሲቀርብ - እያንዳንዱ የውሂብ ተከታታዮች ከበታቻቸው ስያሜ ይሰጣቸዋል። “ቶግሊንግ ቪዚቢሊቲ”፣ የሚለውን በመምረጥ ሁሉንም ተከታታይ ውሂብ ከእይታ ምርጫ ውጪ ማድረግ ይቻላል።
ከዚያም ከቻርቱ በታች የሚገኘውን በስም ለማሳየት የሚፈለጉትን እቃዎች ብቻ ጠቅ ማድረግ ይችላሉ። እርስዎ የመረጧቸውን የውሂብ ተከታታዮች/ጥምረቶችን ለማስተናገድ እንዲችል ስኬሉ በራስ-ሰር ይስተካከላል።

ቶግሊንግ ስታኪንግ

ብዙ ተከታታይ ውሂብ በጊዜ ተከታታይ ቻርት ላይ ሲቀርብ ኦቨርላፒንግ ውሂብን (ከስታክድ የውሂብ ስብስቦች በተቃራኒ) ለማየት የሚያሰችሉ ሁለት መንገዶች አሉ። የመጀመሪያው በማያ ገጹ ግራ ጎን በኩል ያለውን "ኦቨርላፒንግ" ቶግል ቁልፍን መጠቀም ነው። ይህ ለእያንዳንዱ የውሂብ ስብስብ ንጹህ መስመሮች ያላቸው ቻርቶችን ይፈጥራል።
እንደ አማራጭ፣ እያንዳንዱ የውሂብ ስብስብ የራሱ የሆነ የቀለም ሙሌት ያለው ቻርቶችን ለመስራት የሃምበርገር መራጭ "ቶግል ስታኪንግ" አማራጭን ይጠቀሙ። በውሂቡ ላይ በመመስረት፣ የተለያዩ አቀራረቦች የበለጠ ግልጽ ውጤቶችን ሊሰጡ ይችላሉ።

ለሻዶሰርቨር ዳሽቦርድ ልማት የገንዘብ ድጋፍ ያደረገው UK FCDO። ለ IoT መሣሪያ ፊንገርፕሪንቲንግ ስታቲስቲክስ እና ለሀኒፖት ጥቃት ስታቲስቲክስ ከሌሎች አጋሮች ጋር በጋራ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገው Connecting Europe Facility of the European Union (EU CEF VARIoT project) ነው።

በሻዶሰርቨር ዳሽቦርድ ውስጥ ጥቅም ላይ የዋለውን ውሂብ በደግነት አስተዋጽዖ ያደረጉ አጋሮቻችንን፣ እነሱም (በፊደል ተራ)APNIC Community Feeds, CISPA, if-is.net, Kryptos Logic, SecurityScorecard, Yokohama National University እንዲሁም ሌሎች ማንነታቸው እንዳይጠቀስ የመረጡትን ሁሉ ማመስገን እንፈልጋለን።

ሻዶሰርቨር ትንታኔዎችን ለመሰብሰብ ኩኪዎችን ይጠቀማል። ይህም ጣቢያው እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል ለመለካት እና የተጠቃሚዎቻችንን ተሞክሮ ለማሻሻል ያስችለናል። ስለ ኩኪዎች እንዲሁም ሻዶሰርቨር ኩኪዎችን እንዴት እንደሚጠቀምባቸው የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ ድረገፃችንን በ privacy policy ላይ ይጎብኙ። በመሳሣሪያዎ ላይ ኩኪዎችን በዚህ መንገድ ለመጠቀም የእርስዎን ፈቃድ እንፈልጋለን።