ምሳሌ: የኤክስቼንጅ ሰርቨርስ
አጠቃላይ ስታትስቲክስ · ተከታታይ ጊዜ
ባለፈው ሳምንት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ እንደ CVE-2023-36439 ታግ ተሰጥቷቸው በየቀኑ ምላሽ ሲሰጡ የተገኙ የ IPv4 & Ipv6 አድራሻዎች ብዛትን የሚያሳይ ስታክድ ግራፍ።
አጠቃላይ ስታትስቲክስ · ምስላዊ ዕይታ · ሰንጠረዥ
ባለፈው ቀን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ እንደ CVE-2023-36439 ታግ ተሰጥቷቸው በየቀኑ ምላሽ ሲሰጡ የተገኙ የ IPv4 & Ipv6 አድራሻዎች ብዛትን የሚያሳይ ሰንጠረዥ።
አጠቃላይ ስታትስቲክስ · የዛፍ ካርታ
ከሀገር ስፋት ጋር በተመጣጣኝነት በተወከለ ቁጥር፣ እንደ CVE-2023-36439 ታግ ተሰጥቷቸው በተወሰነ ቀን የተገኙ የ IPv4 & Ipv6 አድራሻዎች ብዛትን የሚያሳይ የዛፍ ካርታ።
የሀገር ቁራሽ ክፍል ላይ ጠቅ ማድረግ የሶርሶች ብትን ዝርዝርን ሲደመር አጠቃላይ ስታቲስቲክስን ከ CIA world factbook ላይ ይሰጣል።
ምሳሌ: የተጋለጡ የ CWMP መሣሪያዎች
አጠቃላይ ስታትስቲክስ · ተከታታይ ጊዜ
በሳውዲ አረቢያ በየቀኑ የሚጋለጥ የ CWMP መሣሪያ IP አድራሻዎችን ቁጥር የሚያሳይ የ 2 ዓመት ዋጋ ያለው የታሪካዊ ውሂብ የጊዜ መስመር (በፐብሊክ ዳሽቦርድ ላይ ያለ ከፍተኛው ጊዜ)።
ማስታዎሻ፡- ይህ ግራፍ እ.ኤ.አ በጃንሪ 2023 መጨረሻ ላይ ከ CWMP ተጋላጭነት አንፃር መሻሻልን አሳይቷል።
ምሳሌ: MISP አብነቶች
የ IoT መሳሪያ ስታትስቲክስ · ምስላዊ ዕይታ · የአሞሌ ቻርት
በርከት ያሉ መሣሪያዎች እና የሶፍትዌር ሶልዩሽኖች በስካኒንግ ጊዜ ፊንገርፕሪንት ሊደረጉ ይችላሉ። ይህ ግራፍ የሚያሳየው (በሎጋሪዝም ስኬል) ባለፈው ወር፣ በየአንዳንዱ የ MISP አብነት አሂድ (instances running) በአማካይ በየቀኑ የተገኙ የ IP አድራሻዎችን ቁጥርን ነው።
ምሳሌ: ለብዝበዛ የተዳረጉ ተጋላጭነቶች
የጥቃት ስታትስቲክስ:- ተጋላጭነት · ክትትል
ባለፉት ቀናት የመጀመሪያዎቹ 100 የተገኙ ሙከራ የተደረገባቸው የብዝበዛ ተጋላጭነቶች (ከሀኒፖት ሻዶሰርቨር ማሳያዎች ውስጥ)፣ መጀመሪያ ላይ በልዩ ጥቃት ሰንዛሪ IP’s እንዲደረደሩ የተደረጉ።
የካርታ አማራጩን ጠቅ ማድረግ ተጠቃሚው በ"ሶርስ" እና "መዳረሻ" ሆስት ዓይነቶች መካከል እንዲቀያይር ያስችለዋል (ማለትም በአጥቂው IP ጂኦግራፊያዊ መገኛ እና በሀኒፖት IP ጂኦግራፊያዊ መገኛ መካከል)።
ማስታወሻ፡- የጥቃት ሰንዛሪው ጂኦግራፊያዊ መገኛ የአጥቂውን መገኛ ቦታ በትክክል ሊወክል ወይም ላይወክል ይችላል።
ምሳሌ: ኩነቶችን መተርጎም
ክስተቶችን ለመተርጎም ዳሽቦርዱን መጠቀም፡- ባልተለመደ መልኩ እየጨመረ የመጣ በግብፅ ተጋላጭ ሆኑ የ CWMP መሣሪያዎች (የ Huawei ሆም ራውተሮች እንደሆኑ የሚታመኑ)፣ ይህንንም ተከትሎ ከተመሳሳይ ሀገር የሚነሱ የሚራይ ጥቃቶች።
ማስታዎሻ፡- ሻዶሰርቨር ለማሳወቅ እና የእርምት እርምጃ ለመውሰድ ከግብፅ nCSIRT ጋር ሰርቷል።
የ IoT መሳሪያ ስታትስቲክስ · ተከታታይ ጊዜ
እ.ኤ.አ በ 2023-01-05 እና በዚህ ቀን አካባቢ ይፋ እንደተደረገው በግብፅ መሠረተ ልማት ላይ የተጋለጡ የ IoT መሣሪያዎች መጠን መጨመሩን ምልከታ ተደርጓል።
የ IoT መሳሪያ ስታትስቲክስ · የዛፍ ካርታ በሻጭ
በቀናት ወደ ኋላ እና ወደ ፊት በመሄድ መሣሪያዎቹ የ 2023-01-05 አዲሶቹ ግልፅ የ Huawei መሣሪያዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ያሳያል።
አጠቃላይ ስታትስቲክስ · ተከታታይ ጊዜ
በስካኒንግ ወቅት የታየ የ CWMP ግኝቶች ሹል ከፍታ (spike) በ 2023-01-05 ከተከሰተው ሹል ከፍታ (spike) ጋር ዝምድና/ግንኙነት አለው።
የሻዶሰርቨር ሀኒፖትስ ሴንሰሮች የሚራይ እና ብሩት ፎርስ ጥቃቶችን በመሰንዘር ጥቃት ሊደርስባቸው የሚችሉ የግብፃዊያን መሳሪያዎችን ለይተዋል።
እንዲሁም ከግብፅ ለጥቃት የተጋለጡ መሳሪያዎች የሚሰነዘሩ ተዛማጅ የ ቴልኔት ብሩት ፎርስ ጥቃቶችን ለይተዋል።
ብዙ ሶርሶች መጠቀም እንዲሁም የታግ እና ኦቨርላፒንግ አማራጮችን መምረጥ ምልከታዎቹ በተመሳሳይ ግራፍ ላይ እንዲታዩ ያስችላቸዋል።
ምሳሌ: ልዩ ሪፖርቶች
አልፎ አልፎ ሻዶሰርቨር በዓይነታቸው ልዩ የሆኑ ዘገባዎችን ያወጣል። ውሂቡን በ ኤክስ/ትዊተር እና በድረ-ገፃችን እናሳውቃለን - ነገር ግን ከክስተቱ በኋላ ወሳኝ የሆኑ ቀናትን ማወቅ ይፈልጉ ይሆናል። ቀናቶቹን ለማግኘት የሚቻልበት አንዱ መንገድ በጊዜ ተከታታይ ቻርት ላይ የልዩ ዘገባ ቀኖችን በመፈለግ ይሆናል - እናም እነዚያን ቀኖች ለአንድ ቀን ስታቲስቲክስ ይበልጥ ምቹ ወደሆኑ (እንደ ካርታዎች ወይም የዛፍ ካርታዎች ያሉ) ሌሎች ውክልናዎች ማስተላለፍ ይችላሉ። ልዩ ዘገባዎች በዳሽቦርዱ ላይ የምንጭ ስብስብ special
የሚል ቃል አላቸው።
የጊዜ ተከታታይ ቻርትን በመጠቀም ልዩ ዘገባዎችን መፈለግ፡-
ለምሳሌ የዛፍ ካርታ ልዩ ዘገባ እ.ኤ.አ በ 2024-01-29 ተገኝቷል፡-
ለልዩ ዘገባዎች ዝርዝር እባክዎን የዘገባዎች ዝርዝርን ይቃኙ በእኛ ዋና ድር ጣቢያ ልዩ ዘገባዎች በስማቸው ውስጥ "ልዩ" የሚል ይኖራቸዋል።